image
image
image
image
image

ለመንግስት ሰራተኞች የሰዓት መቆጣጠሪያ የጣት አሻራ አፈፃፀም ዙሪያ ላይ ግንዛቤ ተሰጠ!

ሰኔ 27, 2018
የልደታ ክ/ከተማ የወረዳ 8 አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ሰራተኞች የሰዓት መቆጣጠሪያ የጣት አሻራ አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት አካሂዷል። የወረዳ 08 ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አምባቸው ተፈራ የጣት አሻራ ያስፈለገበት ምክንያት በከተማ አስተዳደሩ በየደረጃው የሚገኙ ሁሉም ሰራተኞች በጣት አሻራ የሰዓት መቆጣጠሪያ ላይ ደረጃውን የጠበቀ፣ አስተማማኝ ፣ቀልጣፋ፣ተጠያቂነት እና ግልፅነት እንዲኖረው ለማድረግ መሆኑን ገልፀዋል ። አቶ አምባቸዉ አክለዉም የጣት አሻራ ከሀምሌ 01/2018 ዓ.ም እንደሚጀምር ተናግረዉ የመንግስት ሰራተኞች በዓመት ፍቃድ በወሊድ ፍቃድ በህመም እና በሌሎች በመስራያ ቤቱ በሚታወቁ ህጋዊ ፍቃዶች በስራ በማይገኙበት ጊዜ ለሰው ሃብት አስተዳደሩ ክፍል በሲስተሙ የቀረበበትን ምክንያት ማረጋገጥ አለበት ፤ሆኖም የታየዘው የጊዜ ገደብ ሲጠናቀቅ ወደ መደበኛ የአሻራ ቁጥጥር ስርዓት እንዲገባ ተናግረዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ የፋይናስ ጽ/ቤት የአይሲቲ ቡድን መሪ አቶ ሰለሞን ታደሰ ሁሉም የወረዳው ቋሚ ሰራተኞች ለአሻራ መስጠት እንዳለባቸው በመግለፅ ሁሉም ሰራተኛ የአተገባበር መመሪያው ተግባራዊ እንዲያደርግ አሳስበዋል:: በዉይይቱ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል ።

መልዕክትዎን ይላኩ