image
image
image
image
image

የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤን መቋቋሙ አገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን ለመፍታት ላቀ ያለ ሚና እንዳለው ተገለፀ።

ታህሳስ 24, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ስርቪስና የሰው ሃብት አስተዳደር ጽ/ቤት በ6 ወር በመማክርት ጉባኤው የተከናወኑ ተግባራት ተገምግሟል። በመድረኩ ከክፍለ ከተማና ከወረዳ የተውጣጡ አስተባባሪዎች ፣ ቡድን መሪዎችና የመማክርት ጉባኤ ስራ አስፈፃሚዎች የተሳተፉ ሲሆን የክ/ከተማው ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት የሪፎርም ክትትልና ድጋፍ ቡድን መሪ አቶ ሙሉጌታ ንጋቱ መማክርት ጉባኤ ያከናወናቸውን ተግባራት ሰነድ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል ። የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ስርቪስና የሰው ሀብት አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ መቅደስ ያደታ እንዳሉት በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት መማክርት ጉባኤው ተገልጋዩንና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማቀናጀት ያሉ አቅሞችን በመጠቀም የአገልግሎት አሰጣጡንና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል አሰራር በመዘርጋ በርካታ ተግባራት መሰራታቸውን ገልጸዋል ። ለተገልጋዮች ፈጣንና ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ መማክርት ጉባኤው ያለው ሚና የጎላ ያሉት ወ/ሮ መቅደስ አያይው አገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ መማክርት ጉባኤው ያለው ሚና የጎላ መሆኑን ገልፀዋል። የመድረኩ ከተሳታፊዎችም መማክርት ጉባኤ መቋቋሙ አገልግሎት አሰጣጡን ላይ የተሻለ ለውጥ እያመጣ እንደሆነ አንስተዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ